የአዲስ አበባ ቁ.2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞች የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪን ጎበኙ፤

Posted in Latest News

 

ባለስልጣኑ እየሰበሰበ ያለው ገቢ በልማት ዕድገቱ ላይ ያለው ድርሻ የላቀ በመሆኑ የገቢ አፈፃፀሙን የበለጠ ለማድረግ ጠንክረው እንደሚሰሩ የአዲስ አበባ ቁ.2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞች የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ በጎበኙበት ወቅት ነበር የገለፁት፡፡

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተጣለበት ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣትና ኢኮኖሚው የሚያመነጨው ገቢ አሟጦ ለመሰብሰብ ጥረት ያደርጋል፡፡ በሚሰበሰበው ገቢ የተለያዩ መሠረተ ልማቶች እውን ይሆናሉ፡፡ ለመከላከያ ሠራዊት አስፈላጊ የሚሆኑ ወጪዎችም ምንጫቸው ከህዝቡ በተሰበሰበው ግብር መሆኑ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ቁ.2 መካከለኛ ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ሠራተኞች በጉብኝቱ ወቅት እንደገለፁት የሚሰበሰበው ግብር በተለያዩ መሠረተ ልማቶች ላይ በግልጽ እየተንፀባረቀ እና የመከላከያ ሠራዊቱን አቅም ከፍ ማድረግ አስችሏል ብለዋል፡፡


ወ/ሮ ሂሩት መብራቴ የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ1.7 ቢሊየን ብር በላይ በሠራተኞቹ ጥረት እንደተሰበሰበና ገቢውም በልማት ላይ መዋሉ አስረድተዋል፡፡

በኢንዱስትሪው እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን ያደነቁት የቅ/ጽ/ቤቱ ሠራተኞቹ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በመሰብሰብ የበለጠ መስራት እንዲቻል የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል፡፡
 

Visitors: Yesterday 805 | This week 4054 | This month 10996 | Total 121952

We have 21 guests and no members online