ከ112ሺ በላይ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎች ሽያጭ እየተከናወነባቸው ነው
ባለስልጣኑ የሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎችን ቁጥር ለማሳደግ እና ሁሉም የንግድ እንቅስቃሴ በሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ እንዲሆን በማድረግ በአገራችን ዘመናዊ የንግድ እና የግብር አሰባሰብ ስርዓት ለማስፈን በርካታ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህም መካከል መሣሪያውን ለማቅረብ ለሚጠይቁ የግል ባለሀብቶች በማስተማርና በመደገፍ የአቅራቢነት እውቅና መስጠት ይገኝበታል፡፡ በመሆኑም በተደረገው ጥረት እስከ የካቲት 30/2007 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ 101ሺ ግብር ከፋዮች 112ሺ የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያዎችን በመጠቀም ላይ መሆናቸውን የታክስ መረጃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የየካቲት ወር ሪፖርት ጠቁሟል፡፡
በኤፍሬም ብላቱ