ባለስልጣኑ የ2006 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀምና የ2007 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ፤

Posted in Tax News

በተጠናቀቀው በጀት አመት ባለስልጣኑ አጠቃላይ የገቢ አሰባሰቡን የተሻለ ለማድረግ በርካታ ስራዎችን በማከናወን አና የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመጠቀም ለማሳካት ካሰበው 101,309.78 ቢሊየን ብር ላይ 98,251.34 በመሰብሰብ የእቅዱን 96.98% ያሳካ መሆኑን በመግለፅ ለተያዘው በጀት አመት የተሻለ ስኬታማ ሊያደርጉ የሚችሉ የመፍትሔ ሀሳቦች ላይ ከነሀሴ 26/2006 ጀምሮ እስከ 30/2006 ዓ.ም ውይይት ተካሂዶአል፤
በተጨማሪም ሁሉም የባለስልጣኑ ሰራተኞች ለግብር ከፋዮች የተቀላጠፈ ፍትሀዊ የሆነ አገልግሎት መስጠት እና ኪራይ ሰብሳቢነትን በቁርጠኝነት መታገል በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሀሳቦችን በማቅረብ የ2007 በጀት አመት የተሻለ የዕቅድ አፈፃፀም ማስገኘት እንዲቻል ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

Visitors: Yesterday 805 | This week 4065 | This month 11007 | Total 121963

We have 26 guests and no members online