ማህሌት ሃብተማርያም
ከካንሰር አጠቃላይ የሞት መጠን አንድ ሦስተኛ የሚሆነው ለመከላከልና ለማስቀረት የሚቻል መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡
ቤዴኩዊላይን በሙከራ ላይ የሚገኝ ባለፉት ሃምሣ ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ አዲስ መድኃኒት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ለሕክምና አገልግሎት እንዲውል የዩናይትድ ስቴትስ የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር ይሁንታ ቸሮታል፡፡
«ከአርባ ስድስት ዓመታት በፊት የአሜሪካ የሰላም ጓድ ሆኜ ወደ ኢትዮጵያ በተጓዝኩበት ጊዜ በኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ስማረክ የተዋወቅኩት ተሥፋዬ ለማ ለኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ ከፍተኛ አስተዋጽ ያደረገ ሰው ነው።» ቻርልስ ሳተን።
በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የኤርትራና የሌሎችም ጎረቤት ሀገሮች ስደተኞች ግብጽ በሚገኘው የሲናይ በረሃ የሚደርስባቸው ወንጀል እንዲቆም የኤርትራው ህዝባዊ ዲሞክራስያዊ ፓርቲ ለግብጹ ፕረዚዳንት ደብዳቤ ላከ።
ኢትዮጵያ በጋዜጦች የተሰኘው ፕሮግራማችን በሳምንቱ ውስጥ ስለ ኢትዮጵያ የተጻፉ የተወሰኑ ጽሁፎችን ጨምቆ ያቀርባል። እስራኤል ከኢትዮጵያውያን አይሁዶች ጋር በተያያዘ አዲስ የወሊድ ቁጥጥር መመርያ አወጣች የሚል ይገኝባቸዋል።
ኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ሕጓን በጋዜጠኞች ላይ አስከፊ በሆነ መንገድ ስለምትጠቀም የጋዜጠኞች አያያዝ ደረጃዋ ቀደም ሲል ከነበረችበት በአሥር መውረዱን ዓለምአቀፉ ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች የሚባለው ድርጅት አስታወቀ፡፡
የኢሀአደግ አራት ድርጅቶች እኩል ናቸው ተብለው የሚታሰቡ እንደመሆኑ መጠን አራቱም ድርጅቶች በከፍተኛው የመንግስት አካል ቦታ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ይላሉ በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር አሰፋ ፍሰሀ።
አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ኦልባና ሌሊሣና ሌሎችም ሰባት ሰዎች እንዲፈቱ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ጫና እንዲያሣድር በመጠየቅ የኦሮሞ ብሔር አባላት የሆኑ ሰልፈኞች ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደጅ ላይ ተገኝተው ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡
የሂዩማን ራይትስ ዋች ሪፖርት ተቀድዶ መጣል ያለበት ሠነድ ነው ሲሉ በአፍሪካ ሕብረትና በመንግሥታቱ ድርጅት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን የኤርትራ አምባሣደር ግርማ አስመሮም ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል፡፡
“በሂደቱ፥ መጀመሪያ ካገኘናቸው ልጆች ጋር ቅርርብ ፈጥረን ስለነበር፥ ሁኔታው ሲሰናከል በእጅጉ ብናዝንም፤ የተለየ አቀራረብ መከተል መረጥን እንጂ፤ ተስፋ አልቆረጥንም።” አቶ ሰለሞን ለማ።
ኤርትራ ውስጥ “በማዕድን ልማት ላይ የግዳጅ ሥራ ይሠማራል፤ በሃገሪቱ ውስጥ የከፋ አፈና አለ” ሲል ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ባለፈው ሣምንት ያወጣውን ክስ ኤርትራ አስተባብላለች፡፡
ወደ አንድ መቶ የሚሆኑ የኤርትራ ወታደሮች ሰሞኑን ባካሄዱት አመፅ የማስታወቂያ ሚኒስቴሩን ይዘውት ውለዋል፡፡ ምሽት ላይ ለቅቀው ወጥተዋል፡፡ ነገሩ ምንድነው? ሰዎቹስ እንዴት ናቸው? ወደፊትስ?
ያመፁ የኤርትራ ወታደሮች የማስታወቂያ ሚኒስቴሩን ለአንድ ቀን ከተቆጣጠሩ በኋላ ለቅቀው መውጣታቸው ተዘግቧል፡፡
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለሁለተኛ የአስተዳደር ዘመናቸው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል፡፡